ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በተለያዩ የድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ኢንተርናሽናል ኮሌጁ በመደበኛ መርሃ ግብር በኹለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 366 ተማሪዎች ነው በስካይላይት ሆቴል ያስመረቀው።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታሪኩ አቶምሳ የኮሌጃችን ስኬት የሚመዘነው በተማሪዎች ስኬት መሆኑን ገልጸው፣ የኮሌጁም ዓላማ ተማሪዎቹ አገርን የሚያገለግሉ፣ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ማድረግ ነው ብለዋል።

ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክትም ለምርቃት መብቃት አንዱ ስኬት ቢሆንም በቀጣይ ለሚኖር ጉዞ መጀመሪያ ነው ብለዋል ።

በዚህ ጊዜ አገራችን ተወዳዳሪ ሆና በራሷ የምትተማመን አገር እንድትሆን መሥራት ይገባልም ነው ያሉት።

በዝግጅቱ ላይ በከፍተኛ ማዕረግ ለተመረቁ 31 ተማሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል። እንዲሁም ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው ዓመቲዊ የተማሪዎች የምርምር አውደ ጥናት ላይ አሸናፊ ለሆኑ አምስት ጥናታዊ ፅሑፍ አቅራቢዎች የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

በምርቃት ዝግጅቱ ላይ ሦስት ተማሪዎች ከየትምህርት ክፍላቸው እጅግ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት የወርቅ ሜዳልያ ሲቀበሉ፤ ከሴት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበች ተማሪም የዋንጫ ሽልማትን ተቀብላለች። በተጨማሪም ከሦስቱም የትምህርት ክፍሎች የላቀ ከፍተኛ ውጤት ላመጣ ተማሪም የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።

የሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ የ2014 ኹለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ለኮሌጁ ኹለተኛ ዙር ተመራቂዎች ሲሆኑ፤ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን፣ በፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በፕሮጀክት ማኔጅመንት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *