የብሩንዲዉ ፕሬዝዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ::

የብሩንዲዉ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ አዲስ ጠቅላይ ሚኒሰትር መሾማቸዉ ታዉቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለምን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሶሙ በግልጽ ባያስታዉቁም የመፈንቅለ መንግስት ስጋት እንዳለባቸዉ ከተነገረ በኋላ መሆኑ ግን ታዉቋል፡፡

የደህንነት ሚኒስተር የነበሩት ጌርቫስ ንድራኮቡካ የብሩንዲ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነዉ በፕሬዝዳንቱ መሾማቸዉ ተነግሯል፡፡

የብሩንዲ ህግ አዉጭዎች በብሩንዲ የሚፈራዉ የቀድሞ የስለላ ድርጅት የቀድሞ ዋና አዛዥ ንድራኮቡካን ሹመት 113-0 በሆነ የፓርላማ ድምጽ አጽድቀዉታል፡፡

በቤዛዊት አራጌ

ጳጉሜ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.