የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂክ ዕቅድ እያዘጋጀሁ ነዉ አለ፡፡

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት በቀጣይ አምስት አመታት በጤና መድህን ዘርፉ ላይ የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂ መተግበር ማስፈለጉን ገልጿል።

በዚህም ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማሳካት የማህበረሰቡን ቋንቋ ፣ባህል ፣ሀይማኖትና አኗኗር ግምት ውስጥ ያስገባ የስትራቴጂክ ዕቅድ መቅረፅ ማስፈለጉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ተናግረዋል።

ከቀጣዩ የጤና መድህን ሥርዓት የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የተናበበ የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት፣ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ባሉ የጤና መድህን ፕሮግራም ተግባራዊ እንደሚደረግም አክለዋል።

የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂው የጤና መድህን ሥርዓቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያቅፍና የጤና መድህን ትምህርቶችና መልዕክቶችን ስታንዳርድ በማድረግና ተደራሽ የሚሆኑበትን ማስተላለፊያ መንገዶችን መርጦ በመጠቀም በማህበረሰቡ ላይ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ መዘጋጀቱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከዚህ በፊት አሰራሩ በኮሚኒኬሽን ስትራቴጂ የታገዘ ስላልነበረ በዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደነበረዉም ተነስቷል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጳጉሜ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *