አቶ ወርቁ አይተነው የአቪዬሽን ኩባንያ አቋቋሙ፡፡

ታዋቂው ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው “ጎልድ ስታር አቪዬሽን ” የተሰኘ የአየር ትራንስፖርት ኩባንያ በማቋቋም ላይ እንደሆኑ ተሰማ፡፡

አቶ ወርቁ ቤል 407 የተሰኘች ሄሊኮፕተር መግዛታቸው የሚታወስ ሲሆን ሄሊኮፕተሯን ወደ ኮሜርሺያል አቪዬሽን እንዳስገቧት ታውቋል፡፡

ባለሀብቱ “ጎልድ ስታር አቪዬሽን ” በሚል ስያሜ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ የመሰረቱ ሲሆን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ፈቃድ (Air operator certificate) ከኢትዮጲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለማግኘት በሂደት ላይ እንደሆኑም ተነግሯል፡፡

አዲስ የተመሰረተው ኩባንያ ተጨማሪ አነስተኛ የአየር ትራንስፖርት አውሮፕላን አስገብቶ የመስራት እቅድ እንዳለው ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
ዘግቧል፡፡

አቶ ወርቁ አይተነው ግዙፍ የሆነውን የደብሊው ኤ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የገነቡ ሲሆን በቅርቡ በአንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመራቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *