ዘመናዊ የከተማ አውቶቡሶች በዛሬዉ እለት ስራ ጀምረዋል።

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከዛሬ መስከረም 9 ቀን 2015 ዘመናዊ ናቸው የተባሉ 110 አውቶብሶችን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታዉቋል፡፡

ነባር እና ዘመናዊ የሆኑትን አውቶቡሶች ጨምሮ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሠጥባቸው የነበሩ 125 መስመሮች ላይ ተጨማሪ 16 መስመሮችን በመጨመር ከዛሬ ጀምሮ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ነዉ የገለጸዉ፡፡

አዲስ ከተከፈቱት መስመሮች መካከል እንደ ቦሌ አራብሳ ፣ የካ አባዶ ፣ ቱሉ ድምቱ፣ በከተማዋ ዳርቻ በሚገኙ ኮንዶሚኒየሞች አካባቢ እና ሌሎችም ስፍራዎች ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ወደ ስራ የሚገቡት እነዚህ አውቶቡሶች በውስጣቸው ሙሉ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን እንደ መጸዳጃ ያሉ አገልግሎቶችን እንደሚሰጡም ነው የተነገረው፡፡
ወደ ስራ ከሚገቡት አውቶቡሶች መካከል ለአካል ጉዳተኞች ተብለው የተሰሩ እንዳሉም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.