የፀደይ ባንክ ስራ መጀመሩን በይፋ አበሰረ፡፡

የቀድሞው የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የአሁኑ የፀደይ ባንክ በይፋ በዛሬው ዕለት የሥራ ማስጀመሪያ ሥነ ስርአት አካሂዷል፡፡

ባንኩ በ8 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል በ148 ቅርንጫፎች በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል።

አብቁተ ወደ ፀደይ ባንክ የተቀየረው የነበሩትን 471 ቅርንጫፎችን ይዞ ነው።

46 ቢሊየን ብር የሚገመት ሀብት ያለው ፀደይ ባንክ ቁጠባ እና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት እንዲሁም የሴቶችን እና የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

አሁን ላይ የፀደይ ባንክ የተፈረመ ካፒታል 7 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ የ10 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው 774 ሺህ 907 አክሲዮኖች አሉት፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *