አትሌት ታየ ግርማ ለአምስት አመት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ታገደ፡፡

አትሌት ታየ ግርማ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት መፈፀሙ በመረጋገጡ ቅጣት ተላልፎበታል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር መኮንን ይደርሳል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ የረጅም ርቀት ሯጭ የሆነዉ አትሌት ታየ ግርማ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ፈፅሞ በመገኘቱ ለአምስት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ መታገዱ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ያስመዘገባቸው ውጤቶች እንዲሰረዙ እና በውድድሮቹ ያገኛቸው ሽልማቶች ተመላሽ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፎበታል ሲሉም አክለዋል፡፡
አትሌቲክሱን ጨምሮ በሌሎችም ስፖርቶች ላይ የሚያካሂደውን ምርመራና ቁጥጥር አጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *