ቤላሩስ በዩክሬኑ ጦርነት ተሳትፎ እንዳላት የሃገሪቱ ፕሬዝደንት አስታወቁ፡፡

ሉካ ሼንኮ አድርገውታል በተባለው ንግግራቸው ሃገራቸው በዩክሬን ጦርነት ተሳትፎ እንደነበራት መግለፃቸው ተዘግቧል፡፡

ሉካ ሼንኮ ተሳትፏችንን አንክድም ሲሉ የገለጹ ሲሆን አንድንም ሰው ግን አልገደልንም ብለዋል፡፡

የቤላሩሱ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አንድም ወታደራዊ ቡድን ወደ ዩክሬን አልላክንም ያሉ ሲሆን ህገወጥ ተግባራትን እንዲሁም የመብት ጥሰቶች ላይ የቤላሩስን ስም ማንሳት ተገቢ አይደልምም ብለዋል፡፡

ሉካ ሼንኮ በዩክሬኑ ጦርነት ሃገራቸው ተሳትፎ አላት ሲሉ ያረጋገጡ ቢሆንም ምን አይነት ተሳትፎ እንዳደረጉ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *