ሞባይል ጠጋኙ ግለሰብ የ20 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆነ፡፡

ነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው ወጣት በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 20ሚሊዮን ብር አሸናፊ መሆኑ ተነግሯል ፡፡

አቶ ማትያስ ግርማ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆነዋል፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በሞባይ ጥገና የሚተዳደሩት የ40 ዓመቱ የ20 ሚሊዮን ብሩ ዕድለኛ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ወረዳ 11 ነዋሪ ናቸው ብለዋል፡፡

ላለፉት 30 ያህል ቀናት እድለኛው ሲፈለግ የነበረ ሲሆን አሁን አሸናፊው መረጋገጡን ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡

ከዚህ በፊትም አስተዳደሩ ለመጀመርያ ጊዜ የ20 ሚሊዮን ብር የእድል ቁጥር ባዘጋጀበት ጊዜም አሸናፊው የታወቀው እጣው ከሚያበቃበት ስድስት ወራት ውስጥ በመጨረሻዎቹ አምስት ቀናት ላይ ነበር፡፡

በሄኖክ ወ/ ገብርኤል

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *