በጦርነት ውስጥ ውድመት እና እልቂት እንጂ አሸናፊነት ባለመኖሩ ሁሉም ሰላምን እንዲያስቀድሙ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን አባ ፍስሃ ታፈሰ ተናገሩ፡፡

አባ ፍሰሃ በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው የሰላም ድርድር ጋር በተገናኘ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም ህወሃት እና የኢትዮጰያ መንግስት በሚያደርጉት የሰላም ድርድር በጎ ነገር እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

ጦርነት ለየትኛውም የአለም ክፍል እልቂትን እንጂ ሰላምን አምጠቶ አያውቅም ያሉ ሲሆን፤ሰላም ለህዝብ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስለሆነም ድርድሩ በአንክሮት በመደማመጥ እና በሰከነ መንፈስ መደረግ እንዳለበት ገልጸው የወንድማማችነት ጸጋ እንዳይጠፋ መጠበቅ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በድርድሩ የሁሉም ብሶት እና ችግር ተደራሽ የሚሆንበት እንዲሁም መፍተሄን በተናጠል ከመፈለግ ይልቅ በጋራ ማድረጉ አቅም እንደሚሰጠት ተናግረዋል፡፡
ስለዚህ ተደራዳሪዎቹ በሃገሪቱ ላለ ለእያንዳንዱ ህዝብ ፍትሃዊ መሆናቸውን በማሳየት ህዝቡ አሁን ካለበት ረሃብ እና ችግር ሊያወጣው የሚገባ ንግግር ማድረግ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

መደማመጥ መንፈሳዊም ዘመናዊነትም በመሆኑ ሁለቱም ወገኖች ድርድር ውስጥ ሊገባ በማይገባው የህዝብ ሰላም ዙሪያ ከስምምነት መድረስ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *