የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለዉይይት በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተገናኝተዋል፡፡

የፌደራል መንግሥቱ መከላከያ ኃይል ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከህወሓት በኩል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ረፋድ ላይ በናይሮቢ ንግግር መጀመራቸው ታወቋል።

የጦር አመራሮቹ የተገናኙት ከቀናት በፊት በሁለቱ አካላት መካከል በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት የማስፈጸም አንዱ አካል በሆነው የትጥቅ ማስፈታት ሂደት ላይ ለመነጋገር ነው።

የንግግሩን መጀመር ይፋ በተደረገበት መድረክ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር ድርድሩን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሱንጉን ኦባሳንጆ እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ተገኝተዋል።

ይህ ውይይት በቀጣይ ቀናት ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *