ሩሲያ ጦሯን ከኬርሶን የማስወጣቱን ስራ ማጠናቀቋን አስታወቀች።

ሩሲያ ስትራቴጂክ ቦታ ከሆነችዉ የኬርሶን ከተማ ለቃ መውጣቷን አስታዉቃለች፡፡

የሞስኮ ባለስልጣናት እንዳሳወቁት ስትራቴጂክ ናት ተብሎ ከሚነገርላት የዩክሬን ዋነኛ ግዛት ከሆነቸው ኬርሶን ለቃ መውጣቷን አረጋግጣለች፡፡

የዩክሬን ባለስልጣናት ኬርሶንን ለመቆጣጠር መቃረባቸውን አሳውቀው ነበር፡፡
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ኦሌስኪ ሪስኮቭ ለሮይተርስ እንዳሳወቁት ኬርሶንን ለመቆጣጠር ጥቂት ስራዎች ብቻ እንደቀራቸው ተናግረዉ ነበር፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዘሌንስኪ የዩክሬን ሀይሎች 41 የሚሆኑ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል አካባቢዎችን ነጻ አዉጥናል ብለዋል፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሩሲያ ጦር በዚህ ደረጃ ማፈግፍግ የመጀመሪዉ መሆኑም ታወቋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ህዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *