የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በመንግሥታቱ የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው ተሾመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሰለሞን አረዳ ከ2023 እስከ 2030 ላለው ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው መሾማቸዉ ታዉቋል፡፡

የዳኝነት ምርጫው የተካሄደው እኤአ ኅዳር 15 ቀን 2022 በኒውዮርክ በተደረገው 34ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ25 ዓመታት በላይ የአገልግሎት ልምድ ያላቸው የህግ ባለሙያ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 07 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *