የአለም የአካል ጉዳተኞች ቀን በድሬድዋ ከተማ ይከበራል፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፌዴሬሽን እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር በጋራ በመሆንም በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡

በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ3ዐኛ ጊዜ ”አካታች የፈጠራ ስራና ሽግግራዊ መፍትሄ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 23 እስከ 24 በድሬድዋ ከተማ ይከበራል ተብሏል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዓሉ በአካል ጉደተኞች ላይ ያለዉን የማህበረሰቡን አመለካከት መቀየር ዋናዉ ዓላማ ያደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አካል ጉዳተኞች በማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ያለመ በዓል ነዉ ሲሉ በመግለጫዉ አንስተዋል።

በዚህ የበዓል አከባበር ከዚህ ቀደም ትኩረት ተነፍገዉ የነበሩ እንደ የአዕምሮ ዕድገት ዉስንት የመሳሰሉ አካል ጉዳተኞች የበዓሉ አካል እንደሚሆንም ተነግሯል

በአቤል ደጀኔ
ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *