በጊዜያዊነት ታገዱ!

በአዲስ አበባ የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት መታገዱ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ታውቋል።

አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት፤ የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ ቢኒያም ምክሩ መግለጻቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም ሃላፊ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *