ሁለተኛ ዙር 12ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 18 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል ተባለ፡፡

ሁለተኛ ዙር 12ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 18 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉም አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡

የሚፈተኑ ተፈታኞች ከሁሉም ክልል ሲሆኑ እነርሱም፡-

  1. የመጀመሪያ ዙር ፈተናን በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት ተንቀሳቅሰው ለመፈተን ያልቻሉ
  2. በህግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው በነበረው መፈተኛ ሁኔታ ለመፈተን ያልቻሉ
  3. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ
  4. በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘና ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል ፈተና ያልተፈተኑ
  5. ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ
  6. በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው
  7. ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው መሆናቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *