አንበሳ ኢንተርናሽል ባንክ እና ሽርሽር ቢዝነስ ግሩፕ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

በስምምነታቸው መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽል ባንክ ሽርሽር ቢዝነስ ግሩፕ ለሚያደርጋቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት የሚያደርግ ሲሆን ሽርሽር አዲስም የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎቹን በአንበሳ ኢንተርናሽል ባንክ በኩል ለማደረግ መስማማታቸውን የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ተናግረዋል፡፡

የባንኮችን የኮር ባንኪንግ ሶሉዩሽን ዓቅም ለማጎልበት ደንበኞችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች የዲጂታል ባንኪግ አገልግሎት በስፋት መስጠት ያስችላል የተባለለት “አለኝታ” የተባለ አነስተኛ የብድር አቅርቦት አገልግሎትም ለማስጀመር ማሰቡንም የባንኩ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዳንኤል ተከስተ ገልፀዋል፡፡

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ታሳቢ በማድረግ በጦርነቱ ተቋርጦ የነበረውን የባንክ አገልግሎት ለማስጀመር የኦዲት ምርመራው እየተጠናቀቀ መሆኑንና በቅርቡ በሁሉም ቅርጫፎቻቸው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመርም የባንኩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

የሽርሽር አዲስ ትሬዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በረከት ባይሳ ዛሬ ድርጅታቸው በደብረ ብርሀን በኤሌትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለመገጣጠም እየሰራ በመሆኑ ባንኩ በዚህ መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ በፋይናንስ ረገድ አጋር ለማድረግ ታስቦ የተፈራረሙት ስምምነት እንሆነ ገልፀዋል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽል ባንክ በአሁን ሰዓት ከ12 ሺህ በላይ ባለ አክስዮኖችና ከ2.6 ቢሊዮን በላይ የተከፈለ ካፒታል ያለው ሲሆን በመላ ሀገሪቱም በሚገኙ 280 ቅርጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት እንደሚገኝም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *