የፈረንሳይ ፖሊስ የተፈጠረውን ችግር በቦታው በመገኘት መቆጣጡሩ የተገለፀ ቢሆንም ስድስት ሰዎች ግን በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልፃል፡፡
በዛሬ ጠዋት ላይ በተፈጠረው ጥቃት ላይ 1 ሰው ክፉኛ ሲጎዳ ሌሎች መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ፓሊስ አሳውቋል፡፡
የፓሪስ ባለስልጣናት እንዳሳወቁት ከሆነ ጥቃት አድራሹ በቦታው በግዳጅ ላይ በነበረ ፖሊስ መምታቱ ታውቋል፡፡
በፈረንሳይ ፓሪስ መዲና ላይ የእንዲህ አይነት ጥቃቶች ተደጋጋሚ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም











