የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ 1 ሺህ 200 በታች እንዲሆን ተወሰነ፡፡

አዲሱን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ አስመልክቶ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የሲሚንቶ አምራቾች ቦርድ በጋራ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የመሸጫ ተመኑ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋልም ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የመሸጫ ዋጋ በኩንታል

ዳንጎቴ ሲሚንቶ 1 ሺህ 106 ብር ከ85 ሳንቲም

ደርባ ሲሚንቶ 1 ሺህ 67 ብር ከ33 ሳንቲም

ካፒታል ሲሚንቶ 1 ሺህ 52 ብር ከ25 ሳንቲም

ኩዩ ሲሚንቶ 1 ሺህ 65 ብር ከ25 ሳንቲም መሸጫ ዋጋ እንደተቆረጠላቸው ተገልጿል።

በአጠቃላይ ሁሉም የሲሚንቶ ምርቶች ከ1 ሺህ 200 ብር በታች እንደሚሸጡ ነው የተገለጸው።

በክልል እና ዞኖችም የመሸጫ ዋጋ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *