የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 13 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2022/23 በጀት ዓመት 88.7ቢሊዮን ተቀማጭ ማሰባሰቡን እና 13 ቢሊዮን ያልተጣራ ብር ማግኘቱን ባንኩ ገልጿል።

ባንኩ በ2022/23 በጀት ዓመት በስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ይህንን እንዳሳካ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል።
ከባንኩ ጠቅላላ እንቅስቃሴም 13 ቢሊዮን ያልተጣራ ብር ማግኘቱን ባንኩ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አቢ ሳኖ የባንኩን የ6ወራት አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን፣ በስድስት ወራት ዉስጥ ከተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ 88.7 ቢሊዮን ተቀማጭ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ የባንኩ አጠቃላንይ ተቀማጭ ሒሳብ በ2022 ከነበረበት 890.1 ቢሊዮን ወደ ብር 978.8 ቢሊዮን መድረሱን ገልፀዋል።

ብድር በማስመለስ በኩል በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት ለሚካሄድ የልማት ፕሮጀክት 55.8 ቢሊዮን ብድር ተመላሽ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

የዉጭ ምንዛሬን በተመለከትም 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሰብሰቡንና የዕቅዱን 11 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።

የገቢና ትርፍ አፈፃፀም ላይም በስድስት ወራት ዉስጥ ከተለያዩ ምንጭች 58.7ቢሊዮን ገቢ መገነቱ ተገልጿል።

በ2ኛ ሩብ ዓመትም የባንኩ ጠቅላላ ሀብተ 1.2 ትሪሊዮን መድረሱ የተለፀ ሲሆን በብር 60 ቢሊዮን አድጓል ተብሏል።

ባንኩ ተደራሽነቱን በማስፋት 55 ኣዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲህን በዚህም የባንኩ ቅርጫፎች 1 ሺህ 879 የደረሱ ሲሆን፣130 አዲስ የሲቢኢ ኑር ወይም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ማስጀመሩንና 1 ሺህ 815 ለዚህ አግልግሎት ክፍት የሆኑ መስኮቶች አዘጋጅቻለዉ ብሏል።

በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት 8.8 ሚሊዮን የኤቲኤም የካርድ ተጠቃሚ እና 6.3 ሚሊዮን የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ደርሰናል ብለዋል።

ባንኩ የዲጂታል አማራጮች አማካይነት ከብር 1.3 ትሪሊዮን በላይ ክፍያዎች መፈፀማቸዉንም የባንኩ ፕሬዝዲንት አቢ ሳኖ ገልፀዋል።

በአቤል ደጀኔ
ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.