የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያጋጠመውን ወቅታዊ ችግር ተከትሎ በመንግስት የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረው ፓስተር ቢንያም ሽታዬ ዛሬ በ5 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ ተወስኗል፡፡
ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው፡፡

ዛሬ ጠዎት ከ3:30 ጀምሮ 33 ጠበቆች በአራዳ ምድብ ችሎት በመገኘት ለፓስተር ቢንያም መከራከራቸውን ቤተክርስትያኗ ያቋቋመችው ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴ አባል የሆኑት ጠበቃ ሙልጌታ በላይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።
ፓስተር ቢንያም ከ14 ቀናት በፊት በመንግስት የጸጥታ አካላት እንፈልግሃለን ተብሎ ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱ መገለጹ አይዘነጋም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም
