በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በምላሻቸውም፦

ሰላምን በተመለከተ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛሬ ስደስት ወር በፊት ከነበረው ዛሬ የተሻለ ሰላም አለ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቆም አንድ እርምጀ ወደፊት የወሰደ ነው፤ ወደ ተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ተኩስ ሲቆም ወዲያውኑ የሰላም ዓየር አይነፍስም፤ ድህረ ግጭት የሚያሳድረው ቁስል ቶሎ የሚሽር አይደለም፤ የጦርነት ነጋሪትን አብዝተው የሚጎስሙ ዜጎች በመኖራቸውም የሰላም ዓየር መኖሩን ለማስብ ያስቸግራል ብለዋል፡፤

ኢትዮጵያ ውስጥ የመጠላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ሲንጸባረቅ ቆይቷል ያሉጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የሚያስፈልገን ግን የሚያስፈልገን የሰላም፣ የይቅርታ መንገድ ነው ሲሉ መልሰዋል።

ሰላምን ማምጣት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን ያሉት ተቅላይ ሚንስትሩ፣ይሁን እንጂ ሰላምን ለማምጣት እንደ ጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል፤ ሰላም ከጦርነት ባልተናነሰ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ሰላም ከጦርነት ያልተናነሰ ትጋት እና ስራን ይፈልጋል፤በተለይም አወንታዊ ሰላም ብዙ ከእኛ ይቅር ከሰላም የምናተርፈው ይበልጣል ብሎ ማመንን ይጠይቃል ብለዋል በምላሻቸው።

ሚዲያን በተመለከተ

ሚዲያን ሰው መርጦ መስማት አለበት፤ ይህ ካልሆነ አላስፈላጊ ነገሮች ይተላለፋሉ፤ አድማጭ ሃላፊነት አለበት፤ ሚዲያ ስለሆነ ብቻ ማዳመጥ አስፈላጊ አይደለም።

የሚዲያ ነጻነት እስከምን ድረስ ነው? የሚዲያ ነጻነት ዜጎችን እስከ ማጫረስ መድረስ የለበትም፤ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን በሚያስራጩበት ጊዜ ሃላፊነት ሊወስዱ እና ሊሰማቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ

“ሰላምን በተመለከተ ከዛሬ ስድስት ወር የተሻለ ሁኔታ አለ።

ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።

ነገር ግን አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ሥራ ተሠርቷል። ጦርነት እንደቆመ ወዲያውኑ ሰላም አይሰፍንም ድኅረ ጦርነት አውድ ጫና አለ።

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ፖለቲካ የመተላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ነበር።

ሰላም አስፈላጊ ነው ብለን በጽኑ እናምናለን። ሰላም እንደጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል።

ከጦርነት ያልተናነሰ ሥራ ድካም ይጠይቃል። የረጋ ሰለማዊ ነገር እንዲሁ አይመጣም አዎንታዊ ሰላም በሀይል አይመጣም። ምንግዜም ሰላም ሲባል የአንድ ሰው ህይወት ማትረፍም ስለሆነ በዚህ ላይ መሥራት ይገባናል። ” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትሩ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

• ከድህረ ጦርነቱ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ሰላምን ለማስፈን ጊዜ ይፈልጋል
• የተሟላ ሰላም ለማምጣት በትብብር መስራት ያስፈልጋል
• የሰላም አየር በተሟላ መልኩ ለማስፈን ጦርነት ጎሳሚዎች የሚፈጥሩት ችግር እንቅፋት ሆኗል
• በአሁኑ ጊዜ ገዳዩ ሰይፍ ሳይሆን የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ ሰይፍ ነው የሚያስፈልገን
• ሰላምን ለማስፈን በይቅርባይነት እና በአዎንታዊነት ደግፈነው በጋራ እውን ለማድረግ በትብብር ልንሰራ ይገባል
• አዎንታዊ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የምክክር፣ የትብብር ተቀራርቦ የመስራት ጅምሮች አሉ፣ ተጠናክሮ ይቀጥላል
• የሰሜኑ ጦርነት በሠላማዊ መንገድ የተደረሰው ስምምነት ወጤታማ ነው
• የሰራ ፖለቲከኞች ሰላም እንዳይፈጠር ይሰራሉ፤ በጉልበት ፖለቲካ የሚያምኑ ሰላም እንዳይፈጠር ይሠራሉ
• ለሠለም ምክክረ ውይይት ለመግባባት ብዙ መድረኮች ተፈጥረዋል የሚሉ ነጥቦችን አነስተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *