የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፦

-በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ብልጽግና አንድ ሆኖ ሁለንተናዊ እድገት ከማምጣት ይልቅ ከመግለጫዎች ጀምሮ ልዩነት ይስተዋላል፣ ችግሩ ምንድን ነው?

-በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የዜጎች መፈናቀል አለ፣ በተለይም ዜጎች ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተከለከሉ ነው፡፡

ሰዎች እየታገቱ ነው፤የታመሙ ሰዎች በጊዜ ለህክምና ባለ መድረሳቸው በመንገድ ላይ ሞተዋል፣ የእህል ምርት ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ እየገባ አይደለም፣ መፈናቀል አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ምን እርምጃ እየተወሰደ ነው፣ በቀጣይስ ምን ታስቧል?

-የዜጎችን ደኅንነት እና የአገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ ሳለ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፤ ቤታቸው ይፈርሳል፤ ንብረታቸውም ይወድማል።

የአገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት አገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርካታ ኪሎሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈጽመዋል።

አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደኅንነትና የአገር ሉዓላዊነት ዋነኛ የስጋት ምንጭ ሆኖ የምናየው ራሱ መንግስትን ነው። እርስዎ በአፍዎ «ኢትዮጵያ አትፈርስም» ቢሉንም በተግባር ግን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በመንግስትዎ እየተናዱ ነው።

የበርካታ አገራት መሪዎቸ መሰል ኃላፊነትን በወጉ ያለመወጣት ጉድለት ሲያሳዩ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው ሥልጣናቸውን ሲለቁ ይታያል፤እርስዎስ?

-የህዳሴው ግድብ ግንባታ ያለበት ሁኔታና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የሚደርሱ የፖለቲካ ጫናዎች እንዴት ይታያሉ?

-ቀደም ሲል ስለ ፍትሃዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት በእጅጉ ሲነሳ ቆይቷል፤ይህ ጥያቄ አሁንም አልተፈታም፤ምክንያ ምንድን ነው? የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.