በኢትዮጵያ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከገደል አፋፍ ላይ ይገኛል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቋርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የአለም የሰብዓዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በ412 ገፆች የተቀነበበ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በከፍተኛ ሁኔታ መሸርሸሩን ጠቅሶ፣ በትግራይ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ29 ያላነሱ ጋዜጠኞችን እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ታስረው እንደሚገኙ አስታውሷል፡፡

ሪፖርቱ በመጋቢት ወር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ምርመራ ለማካሄድ እና ግድያውን የፈፀሙትን ለፍርድ ለማቅረብ ቃል የገባ ቢሆንም፣ በአመቱ መጨረሻ ድረስ ስለ ምርመራ እና የክስ ሂደቶች ምንም አይነት መረጃ ይፋ አለመደረጉን አክሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *