በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ንብረቶች ከ66.1 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የመንግስት ግዥ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጎጃም ታደለ ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል።

በፌዴራል መ/ቤቶች እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸው ንብረቶች 22 ፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች 44 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በማስወገድ እንዲሁም የ19 ፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች 198 ሎት ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ገቢ ማስገኘት የተቻለ ሲሆን በድምሩ በዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

በበጀት አመቱ 53.8 ሚሊየን ብር ገቢ የማግኘት እቅድ እንደነበራቸው የሚናገሩት ሃላፌዋ ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ብልጫ ማሳየቱም ተመላክቷል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.