በከተማዋ 80 በመቶ የመኪና አደጋ እግረኞች ላይ የሚደርስ ነዉ ተባለ።

ከ2009 ዓ.ም  ጀምሮ በትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስተባባሪነት የ13 ዓመት የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በመንደፍ በከተማዋ ከንቲባ የሚመራ የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት መቋቋሙ የሚታወስ ነዉ።

የ2015 በጀት ዓመት የ6ወራት የትራፊክ አደጋ መረጃ  በብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አስተባባሪነት የመረጃ ትንተና ተካሂዷል።

ወ/ሮ ሜሮን ጌታቸዉ  በብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ የዳታ ትንተና ባለሙያ እንደገለፁት ከሆነ 703ሺህ የተመዘገበ ተሽከርካሪ በከተማዋ ይገኛል ብለዋል።

በከተማዋ ከሚፈፀሙ የመኪና አደጋዎች 80 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ እግረኞች ላይ ነዉ ብለዋል።

ከሚያጋጥሙ የሞት አደጋዎች 78 በመቶ ወንድ ሲሆን 22 በመቶ የሚሆነዉ የሞት አደጋ ሴቶች ላይ የሚያግጥም መሆኑን ተገልፃል።

ጥናቱ በከተማዎ 20 የተለያዩ  አደጋ የሚያግጥማቸዉ ቦታዎችን ለይቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበዉ ሚደቅሳ  በከተማዋ በስድስት ወራት ዉስጥ 211 ሰዎች ህይወት በመኪና አደጋ ማለፉን ገልፀዉ ከሞቾች ዉስጥም በአብዛኛዉ ከ20 እስከ 49 ዕድሜ ክልል ያሉት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የመንገድ ደኅንነት ምክር ቤቱ  የምክር ቤቱ አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣አርቲስቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካለት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

አቤልደጀኔ
ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.