ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ ወደ ፍርድ ቤት ደርሰው በዋስትና ከሚወጡ ሰዎች መካከል በሚመጡ ዛቻ እና ማስፈራሪያ መቸገሩን የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መኑር መሃመድ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀላፊው ገለጻ ከሃሰተኛ ሰነዶች ጋር በተያያዘ ክትትል እና ፍተሻ ሲደረግ እንደሚገኙ ና ተጠርጣሪ ሰዎችን ወደ ህግ ወስዶ ጉዳዩ ላይ ወሳኔ እስኪሰጠው ክትትል የማድረግ ስራ እንደሚሰሩም አቶ መኑር ነግረውናል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት በፍትህ ሂደቱ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ የሚታሰርበት መንገድ እንደሌለ አስታውሰው ሰዎቹ በዋስትና ሲለቀቁ የማስፈራራት እና ዛቻ መሰል ጉዳዮች እየመጡ ተቸግረናል ስራችንንም እየረበሸው ነው ብለዋል፡፡
ረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም
