ኢትዮ ኢንተርናሽናል ኤክስፖ ሊዘጋጅ ነው።

በአምስት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገው ኢትዮ – ኢንተርናሽናል ኤክስፖ ሊካሄድ ነው።

ኤክስፖውን ትሬድ ኢትዮጵያ ከአዲስ እይታ እና ከአቡቀለምሲስ የሪል ስቴት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን አዘጋጅቶታል ተብሏል።

ኤክስፖው በግብርና ፣ ሪል ስቴት ፣ በታዳሽ ሃይል እና ኤሌክትሪክ መኪና ፣ በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትኩረት ማድረጉን የትሬድ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ በርናባስ ወ/ገብርኤል ተናግረዋል ።

ኤክስፖው በአመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በአሜሪካ የሚካሄድ ነው ተብሏል።

ባለፈው አመት በኦንላይን ብቻ ይሄ ኤክስፖ ተካሂዶ ነበር ያሉት አቶ በርናባስ በዚህ አመት ለ3 ቀናት በአካል ከተካሄደ በኋላ ለቀጣይ 5 ወራት ደግሞ በኦንላይን ይቀጥላል ነው ያሉት ።

በኤክስፖው ላይ 25 ሺህ ቤት ፈላጊ ዲያስፖራዎች ይሳተፉበታል የተባለ ሲሆን ካሉበት ሆነው በኦንላይን ኤክስፖውን በመሳተፍ የሚፈልጉትን ቤት ማማረጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ኢንተርሌግዥሪ ሆቴል ከግንቦት 9-11 የሚካሄድ ሲሆን በገዢ እና በሻጭ መካከል ያለውን የግብይት ክፍተት በመሙላት የማስተሳሰር ስራ ይሰራበታል ተብሏል።

እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *