የዉጭ ሃይሎች ከሶሪያ ምድር እንዲወጡ የአረብ አገራት በጋራ ጠየቁ፡፡

የአረብ ሃያላን አገራት የዉጭ ሓይሎች ከሶሪያ ምድር እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የሳዉዲ አረቢያ፤የግብፅ ፡የጆርዳን፤ የኢራቅና የሶሪያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ፣የዉጭ ሃይሎች በፍጥነት ከደማስቆ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

አምስቱ አገራት በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሃይሎች ቀጠናዉን እያመሱት ነዉ ሲሉም ከሰዋል፡፡

ሶሪያን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ያስታወቁት አገራቱ ፤ በቅድሚያ ግን እነዚህ ሓይሎች ደመስቆን ለቀዉ መዉጣት አለባቸዉ ማለታቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በሶሪያ ምድር በርካታ አገራት በእጅ አዙር ጦርነት ዉስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በአባቱ መረቀ

ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *