ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ ታጣቂዎች በጋምቤላ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ የሚፈፅሙት ዝርፊያ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡

ከሰሞኑን በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የዘረፏቸውን ከ 1 መቶ በላይ ከብቶች ማስመለሱን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡

ድንበር ተሸግረው የመጡ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የዘረፏቸውን ከ 1መቶ በላይ ከብቶች ማስመለስ የተቻለው ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ነው፡፡

ከታጣቂዎች ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከስድስት ያላነሱ ከብቶች ሲገደሉ ሌሎቹን በማስጣል ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ም/ ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለ ኢትዮ ኤፍኤም አስታውቀዋል፡፡

ከደብቡ ሱዳን የሚነሱት ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ወደ ክልሉ የድንበር ወረዳዎች በመግባት ህፃናትን ጨምሮ፤ ከብቶችን በመዝረፍ እና ጥቃት በማድረስ ህገወጥ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ይፈፅማሉ ብለውናል፡፡

በሌላ ዜና በክልሉ ባለፉት ቀናት ከህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከ 30 በላይ ክላሽኮፕ መሳሪያ መያዙንም አቶ ኦኮት ነግረውናል፡፡

የውልሰው ገዝሙ

ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *