ቢሾፍቱ ከተማን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ጌታቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከተማዋን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ የማሳደግ ስራ እየተሳራ ሲሆን አወቃቀሯንም በመቀየር እንደ አዳማ እና ሻሸመኔ ሁሉ ቢሾፍቱም በክፍለ ከተማ እና ወረዳ እንድትደራጅ መደረጉን አንስተዋል።

ቢሾፍቱ ከበፊት ስፋቷን በመጨመር አምስት ትናንሽ ከተሟችን ወደራሷ በመቀላቀል 1ሺ 52 ሄክታር ስፋት እንዲኖራት መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የቢሾፍቱ ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የቢሾፍቱ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ለዚህም ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታውቆ፣ ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ጠቅሶ ነበር፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *