በ35 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ በህገወጥ መንገድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሆቴሎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ያልተገባ አገልግሎት እየሰጡ በተገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ህጋዊ እርምጃ አየተወሰደባቸው ይገኛል ብለዋል።

ሆቴሎቹ ሺሻ ሲያስጠቅሙ የተገኙ ሲሆን በዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳትፈው የተያዙ 1ሺህ 250 ሰዋች መያዛቸውንም ተናግረዋል።

በተያያዘ የህግ ማስከበር ዜና

ህገ-ወጥ በሆኑ ጫኝና አውራጆች ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ለህብረተሰቡ ችግር የሆኑ በመዲናዋ በጫኝ እና አውራጅ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በማህበር ተደራጅተው ዜጎችን ያላግባብ በሚያስከፍሉት ላይ እርምጃ እየወሰድን እንገኛለን ብለዋል።
እነዚህ ሰዎች ነዋሪዎች በሃገራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጉ ናቸውም ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *