በሊባኖስ የሶሪያ ድንበር አቅራቢያ የተፈፀመውን ጥቃት የእስራኤል ሀይሎች እንደፈፀሙት ሲገለፅ፣ ከእስራኤል አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ግን ጥቃቱን እስራኤል እንዳልፈፀመች የሚያስተባብሉ ናቸው፡፡
የፍልስጤም ነፃ አውጪ ግምባር እንዳስታወቀው በምስራቅ ሊባኖስ በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በፍዳታው አምስት አባላቱ እንደተገደሉበት ገልጾ ለፍንዳታውም እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል፡፡
አንዋር ራጃ የተባለ የነፃ አውጪው ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው፣ በተፈፀመው በእስራኤል ጥቃት አስር የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን፣ ሁለቱ በከባድ የህክምና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከእስራኤልም ሆነ ከሊባኖስ ተሰጠ ይፋዊ መረጃ እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም











