በትግራይ ክልል 552 ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ አገልግሎት መስጠት አለመጀመራቸው ተገለፀ፡፡

በክልሉ ከሚያዚያ 23 2015 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምር መደረጉ የተገለፀ ቢሆንም አሁንም በርካታ ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት መመለስ አልቻሉም ተብሏል፡፡

የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዕሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በክልሉ ከነበረው 1774 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 552 የሚሆኑት አሁንም ድረስ አገልግሎት መስጠት አለመጀመራቸውን ነግረውናል፡፡

ሀላፊው ለዚህ እንደምክንያት ያነሱት በማዕከላዊ ዞን ትግራይ 12 ትምህርት ቤቶች፣በሰሜን ምዕራብ ትግራይ 15 ትምህርት ቤቶች በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ያሉ በመሆናቸው ትምህርት ማስጀመር እንዳልተቻለ አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስር የነበሩ አካባቢዎች የሚገኙ የነበሩ በርካታ ትምህርት ቤቶችን ወደ አገልግሎት ማስመለስ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ኪሮስ ከነዚህ ምክንያቶች በተጨማሪ በርካታ ተፈናቃይ ወገኖች በተለያ የትግራይ አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶች በመጠለላቸው ትምህርት ቤቶቹ አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም በነዚህ 552 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለመቻሉን ለጣብያች ገልፀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.