ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ በ 60 ዓመታት ውስጥ ከ 2 መቶ ሺህ በላይ የሰው ሃይል አሰልጥኖ ማስመረቁን አስታወቀ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

ዩንቨርስቲው የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የቀድሞ ምሩቃንና የ 60ኛ ዓመት በዓል አስተባባሪ አቶ ታምሩ ደለለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ዩንቨርስቲው ከ 2 መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ዩንቨርስቲው በ 60 ዓመታት ጉዞው በተለያዩ የትምህርት መስክ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በማስመረቅ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት ችሏል ነው ያሉት።

ዩንቨርስቲው ከግንቦት 28/2015 እስከ ሰኔ 04 2015 ዓ.ም ድረስ የምስረታ በዓል የመዝጊያ ሳምንት እያከበረ እንደሚገኝ ታውቋል።

በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንቶች፣ምሩቃንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል።

በዓሉ በጥናታዊ ፅሁፎች፣በአውደ ርዕይ፣ በፋሽን ሾው፣ በምስጋናና በስፖርታዊ ክንውኖች በድምቀት እንደሚያከበርም የበዓሉ አስተባባሪ አቶ ታምሩ ደለለኝ ተናግረዋል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *