ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ጅቡቲ ገብተዋል፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች “ወሳኝ” የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት በጅቡቲ እየተሰባሰቡ ነው፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች ለ14ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ በጅቡቲ ዋና ከተማ ጅቡቲ ተገናኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ጅቡቲ ገብተዋል፤ ኤርትራ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኦስማን ሳሌህ ተወክላለች፡፡

በጉባኤው መሪዎቹ የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ልማት በሚመለከቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

የኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎችን ያሳተፈዉ ጉባኤ የአፍሪቃ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮችን እንደሚያስተናግድም ተሰምቷል፡፡

ልዑካኑ በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ ክልላዊ ውህደትን ማጎልበት፣ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን፣ የኢኮኖሚ እድገትና ማህበራዊ ልማትን ማጎልበት በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሉ በግጭቶች እና ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋቶችን ጨምሮ ከበርካታ ተግዳሮቶች ጋር እየታገለ ባለበት ወቅት የሚደረግ ጉባኤ በመሆኑ “ወሳኝ” ነው ሲል ኦል አፍሪቃ ዘግቧል።

በያይኔ አበባ ሻምበል

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *