ስለ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መረጃዎች፤

 በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከ70 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ይሆናል ተብሏል

 በአሁኑ ወቅት ስራው እየተሰራ የሚገኘው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ስር ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ 1284/2015 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ ተገብቷል።

 ይህም ስርዓት “አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል መርህ የሚተገበርና ግለሰቦችን በስነ-ህዝብ እና በባዮ ሜትሪክ ማረጋገጫዎች ለመለየት የሚያስችል ነው።

 ምዝገባው ሲካሄድ የስነ-ሕዝብ መረጃዎች ስም፣ ፆታ፣ ዕድሜ፣ አሁናዊ የመኖሪያ አድራሻ፣ ዜግነት እንዲሁም የባዮ ሜትሪክ መለያ የሚባሉትን የጣት አሻራ፣ የዓይን ብሌንና የፊት ገፅታ መረጃዎች ብቻ ያስፈልጋል፡፡

 እስካሁን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አካሂዷል።

 የቴሌብር ሱፐር አፕ እና የብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ መተግበሪያ ስለተሳሰሩ ማንኛውም ተመዝጋቢ የቴሌብር መተግበሪያን በመጠቀም የዲጂታል መታወቂያውን ማግኘት ይችላል።(ኢፕድ)

ሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *