ዛሬ ማለዳ በተከሰተ የእሳት አደጋ 21 ሱቆች ተቃጥለዋል፡፡

ዛሬ ማለዳ 1:50 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሰፈራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 21 የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል።

በእሳት አደጋዉ ጉዳት የደረሰባቸዉ ልዩ ልዩ የንግድ ስራዎች የሚከናወባቸዉ ናቸዉ።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 11 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር እንዲሰማሩ ተደርጓል።

የንግድ ቤቶቹ የተገነቡበት ቁሳቁስና ቤቶቹ ተጠጋግተዉ መሰራታቸዉ እንዲሁም ለአደጋ ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮች መኖራቸዉ የእሳት አደጋዉ በቀላሉ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሶስት ሰዓት በፈጀ የአደጋ መቆጣጠር ስራ እሳቱ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *