ለሱዳን ቀውስ ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከለጋሾች መገኘቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ 2.57 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል እያለ ነው።

ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችም ለሱዳን ሰብአዊ ቀውስ የሚውል እና ጦርነቱን ሸሽተው ለሚሰደዱ ለጎረቤት ሀገራት 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሀገራት ለሱዳን እርዳታ እንዲያደርጉ ጥየቄ ማቅረቡ ይታወሳል።

በአስር ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ለመስጠት ቃል ከገቡት ሀገራት መካከል፣ ጀርመን፣ ኳታር፣ ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ቀዳሚዎቹ ናቸው።

ወደ 24.7 ሚሊዮን የሚሆነው የሱዳን ህዝብ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሏል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት።
ከሱዳን ወደ 2.2 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ቤት ንብረታቸው ጥለው መሰደዳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በየውልሰው ገዝሙ
ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *