በተባበሩት ምንግስታት ድርጅት አለም አቀፍ ዳኛ ሆነው የተመረጡት አቶ ሰለሞን አረዳ በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
የቀድሞ የፌደራል ፍርድ ቤት ምክትል ዳኛ የነበሩት እና በገዛ ፍቃዳቸው ስራቸውን የለቀቁት አቶ ሰለሞን አረዳ አሁን በተባበሩት መግስታት ድርጀት በአለም አቀፍ ዳኝነት የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡
ዓለምአቀፍ ዳኛ ሆነው የተመረጡት ሰለሞን አረዳ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉትይሬዝ ፊት ቃለ-መሀላ ፍፅመው ስራ ጀምረዋል።
አቶ ሰለሞን አረዳ በድርጅቱ ለሚቀጥሉት ሰባት አመታት በዳኝነት የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ በይፋዊ የቲውተር ገጹ ባሰፈረው ጹሁፍ እንዳስነበበው ከሆነ አቶ ሰለሞን በክርክር ዳኝነት ድርጅቱን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ያገለግላሉ ብሏል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም
