ዚምባብዌ በምርጫ ለመወዳደር የሚጠየቀው ክፍያ የፓርቲ አባላት ቁጥር እንዲቀንስ እያደረገው ነው ተባለ፡፡

የዚምባብዌ ምርጫ ኮሚሽን በነሀሴ ወር ለሚካሄደው ምርጫ አንዳንድ እጩዎች የምዝገባ ክፍያ እስከ 20 ሺህ ዶላር በጥሬ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ መሆኑ እያነጋገረ ይገኛል፡፤

ዚምባቡዌ በዶላር እና በአገር ውስጥ ምንዛሪ የገንዘብ እጥረት አጣብቂኝ ውስጥ እንደምትገኝ ቢቢሲ አፍሪካ አስነብቧል፡፡

በዚህ ሳቢያ ጥቂት የሚባሉ አባላት ካሏቸው ፓርቲዎች የተወከሉ እጩዎች ቀድሞ ከነበረው በ20 እጥፍ የመመዝገቢያ ክፍያ በመጨመር የእጩዎችን ቁጥር እየቀነሰው ነው ሲሉ የፓርቲ ተወካዮች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በ2018 ከነበረው 1ሺህ ዶላር ክፍያቸው ወደ 20 ሺህ ዶላር አሳድገው እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡

ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ከሚፈልጉት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ይህ በዶላር እና በጥሬ ገንዘብ እጥረት ሳቢያ የተፈጠረ በማስመሰል፤የተወዳዳሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ እና መራጩን ለመከፋፈል የታሰበ ሴራ ነው ብለዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *