ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሲኖትራክ የተገጨው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ::

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ሰኔ 23 ከቀኑ 6:00 ገደማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታዉ ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት በሲኖትራክ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት፣ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_ኢት A04091 የሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ፣ መንገድ በመሻገር ላይ ያለ ዕድሜዉ 50 ዓመት የተገመተ ሰዉ ገጭቶ ህይወቱ አልፏል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተሽከርካሪዉ ተገጭቶ ህይወቱ ያለፈዉን ግለሰብ አስከሬን ከተሽከርካሪዉ ስር በማሸነሪ ታግዘዉ እንዳወጡትም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *