‹‹በመንግስት በጀት የተሰሩ 130 ሺህ ኮንዶሚኒየሞች በዚህ ክረምት ለተጠቃሚ እናስረክባለን፡፡

››ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
በአዲስ አበባ በመንግስት በጀት የተሰሩ 130 ሺህ ኮንዶሚኒየሞች እና 5 ሺህ ቁጠባ የኪራይ ቤቶች ተሰርተዉ ማለቃቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ቤቶች በዚህ ክረምት ለነዋሪዎች እናስረክባለን ነዉ ያሉት፡፡
በመንግስት የሚሰራዉ በመንግስት በጀት፣ በልመና የሚሰራዉ በልመና እንዲሁም ደግሞ በትብብር የሚሰራዉ በትብብር ይሰራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደዚህ ዓይነት ስራዎችን መደገፍ ካልቻልን ዝም ማለት ይሻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለዉጡ በፊት 3መቶ ሺህ ዳቦ ይመረት ነበር ያሉ ሲሆን አሁን ግን 4ሚሊየን ዳቦ የማምረት አቅም አለን ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በቀን 2መቶ 80ሺህ እንጀራ መጋገር የሚችል ፋብሪካ ሰርተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ቁጥሩን ብንጨምር የአዲስ አበባን 20-30 በመቶ ህዝብ እንጀራን እንደ ዳቦ በማንኛዉም ሰዓት ገዝተዉ እንዲመገቡ ማድረግ እንችላለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *