በክልሉ የሚገኙ የቀድሞ የፖሊስ አባላት ከብልፅግና ፓርቲ ደሞዝ ስትቀበሉ ነበር በሚል እና የትጥቅ ትግሉን አልተቀላቀላቹም በማለት ከስራ እና ከደሞዝ እንዲታገዱ እንደተደረገ ቅሬታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አቅርበዋል፡፡
እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች እስከ 30 ዓመት ድረስ በተለያዩ የትግራይ አካባቢ ተመድበው በፖሊስነት ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት፥ ከስራ እና ደመወዝ ውጭ እንዲሆኑ የተደረጉት ከጦርነቱ ጅማሮ በኃላ ባለው ጊዜ መሆኑ ነግረውናል።
እንደ ፖሊሶቹ ገለፃ በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ መከላከያ ትግራይን ሲቆጣጠር አቋቁሞት በነበረው ግዚያዊ አስተዳደር ጋር አብራችሁ ሰርታቹሀል የመንግስትን ደሞዝም ተቀብላቹሀል በሚል መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በ2013 ዓ.ም በርሃ የነበረው የህውሀት ምክር ቤት በዶ/ር ድብረፅዮን ፊርማ በተረጋገጠ ደብዳቤ ነባሩን የፖሊስ አባል በመሰረዝ አዲስ ማቋቋሙን በመግለፅ ከህግ ውጪ ያለ ስራ እንዲቀመጡና ለከፋ ችግር እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡
ነባር የፖሊስ አባላቱ በተደጋጋሚ የፖሊስ ኮሚሽን በመቅረብ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡን የተሰጣቸው ምላሽ ኮመኪሽኑ እነሱ መበተናቸውንና አዲስ የተቋቋመውን አባላት እንደሚያውቅ እንዳሳወቃቸውን ይናገራሉ፡፡
ጣብያችን የፖሊስ አባላቱን ቅሬታ በመያዝ በኢትዮጵያ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ቅርጫፍ ግዚያዊ አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ፀሀዬ እምባዬን የፀየቀ ሲሆን እሳቸውም ፖሊሶቹ አንድ ደብዳቤ ከኮመኪሽኑ እንደተሰጣቸው ነግረውናል፡፡
ተቋሙ በአሰራሩ መሰረት ሁሌ ደረጃ መሄድ ስላለበት ፖሊሶቹ ከግዚያዊ አስተዳደሩ የሚሰጣቸው ምላሽ ከተመለከተ በኃላ ወደ ምርመራ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
ከ200 በላይ የሚሆኑት እነዚህ ነባር የፖሊስ አባላት በአሁን ሰዓት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውንና የሚመለከተው አካል ምላሽ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
