የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኒጀርን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት አገደ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ኒጀርን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ለማገድ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ፣ የኒጀርን የአፍሪካ ኅብረት ተሳታፊነት እና አባልነት በአስቸኳይ እንዲታገድ ሲል ወስኗል።
ባሳለፍነው ሀምሌ 26/2015 በኒጀር ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ምክር ቤቱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ በኢኩዋስ ለሚደረገውን ጥረት አጋርነቱንም አረጋግጧል።

ህብረቱ መፈንቅለ መንግስቱን ያካሄዱ ወታደሮች የኒጀርን ህዝብ ጥቅም ከምንም በላይ እንዲያስቀድሙ እና በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኒጀር ህገ መንግስት ጋር በተጣጣመ መልኩ ለሲቪል ባለስልጣናት ስልጣኑን እንዲያስረክቡ አሳስቧል።
ምክር ቤቱ በአህጉሪቱ የሚካሄድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያገረሸ መሄዱ በእጅጉ እንደሚያሳስበው መግለጹንም ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

ነሃሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *