“ግጭቶች ሳይፈጠሩ ቀድመን ወደ ውይይት መምጣት አለብን፣ እሣት ማጥፋት ላይ መጠመድ የለብንም” ሲሉ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /ካርድ/ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ሀይሉ ተናገሩ፡፡

የነበሩ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለምፍታት፣ እየመጡ ያሉ የሚታዩ ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከልና መልስ እንዲያገኙ ለማድረግ እና በሰላማዊ መንገድ የተፈቱ ግጭቶችን ዛላቂ ለማድረግ ሁሉን አካታች የውይይት መድረክ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሀገራችን እስካሁን ድረስ እየተደረጉ ያሉት ሙከራዎች እሣት የማጥፋት ሁኔታዎቸ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬከተሩ የውይይት መድረኮች ግጭቶች ሳይፈጠሩ ቀድመው መከናወን አለባቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ አቅጣጫዎች ግጭቶች ሲመጡ ቀድመው ይታያሉ ስለዚህም እነዚህን ግጭቶች ለመከላከል የሚያስችል የውይይት መድረክ ያስፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በትግራይ የነበረው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቅርበን ከመንግስት ከፍተኛ ውግዘትን ብናስተናግድም ከተወሰኑ ወራት ባኃላ የፕሪቶሪያው ውይይት ተካሂዷል ብለዋል አቶ በፍቃዱ ሀይሉ፡፡

በመሆኑም መንግስት አሁንም ሁሉን አቀፍ የሆነና ዘላቂ የሆነ መድረክ አዘጋጅቶ ያሉበትን ችግሮች በውይይት መፍታት ያስፈልገዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ጳጉሜ 02 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.