በመዲናዋ የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ መከበሩ ተገለጸ፡፡

የ2016 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በዋዜማውም ሆነ በበዓሉ ዕለት እሳትና መሰል አደጋዎች ሳያጋጥሙ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ በዓሉ ከመድረሱ በፊት በተለያዩ አማራጮች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጉ፣ በዓሉ ያለ ምንም አደጋ በሰላም መከበሩን አመልክተዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህብረተሰቡና የሚዲያ ተቋማት አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናውን በማቅረብ፣ በቀጣይ በሚኖሩ በዓላትና በመደበኛ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተመሳሳይ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ ጥሪውን አቅርበዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 02 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *