በሊቢያ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ11 ሺህ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

በሀገረ ሊቢያ ደርና ከተማ በተከሰተዉ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 11 ሺህ 3 መቶ መድረሱ ተነግሯል፡፡

የሀገሪቱ ቀይ መስቀል እንዳስታወቀዉ፤ ከሟቾች በተቸማሪም 10 ሺህ አንድ መቶ ዜጎች የት እንደደረሱ አልታወቀም፡፡

የባህር ዳርቻ ከተማ የሆነችዉ ደርና በጎርፍ አደጋ ተጥለቅልቃ ክፉኛ ተጎድታለች፡፡

የደርና ከተማ ከንቲባ አብደል ሞኒም አል ጋኢቲ የሟቾች ቁጥር ከ20 ሺህ ሊበልጥ እንደሚችል መናገራቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

የሞቱት ዜጎችም በጅምላ እየተቀበሩ መሆኑን ዘገባዉ አስፍሯል፡፡

በአባቱ መረቀ

መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *