በአማራ ክልል የቀጠለው ጦርነት አርሶ አደሩ ተረጋግቶ የግብርና ሥራውን እንዳይሠራ እና መደበኛ ሕይወቱን እንዳይመራ አድርጎታል—-ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ሁኔታ የተመለከተ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡

ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን፣ ኮሚሽኑ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራዎች የተዘጋጀ ነው፡፡

በሪፖርቱ በአማራ ክልል በቀጠለው ጦርነት ምክንያት አርሶ አደሩ ተረጋግቶ የግብርና ሥራውን እንዳይሠራ እና መደበኛ ሕይወቱን እንዳይመራ አድርጎታል ብሏል፡፡

ግጭቱ ይህ ሪፖርት ይፋ በተደረገበት ወቅትም የቀጠለ እና እልባት ያልተበጀለት በመሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሱ መባባሱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል፣ በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግር እና እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት፣ የመሥራት፣ ከሚኖሩበት ቦታ ያላግባብ በኃይል ያለመፈናቀል እና ንብረት የማፍራት መብቶችን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው በአሳሳቢነት ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ናቸው።

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጸጥታና ደኅንነት ሥጋት በሚል እና በሌሎች ምክንያቶች የንግድና የመኖሪያ ቤቶች በማፍረስ ሂደት ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች ሳይቀር የንግድ ቤቶቻቸው ያላግባብ እንዲፈርሱ መደረጉና ንብረታቸው መወሰዱ በገቢያቸውና በኑሯቸው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *