ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ግጭቶች መቋጫ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አስታወቀ።

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የምሁራን ትብብር ዲሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ላይ አተኩሮ እንደሚሰራም አስታወቋል።

ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣የምርምር ተቋማት ከአካዳሚያ አጠቃላይ በጋራ መስራታቸዉ ለሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር አስታዋፅአቸዉ ከፍተኛ እንደሆነ ተገልፃል።

በሀገሪቱ በዚህ ሰዓት እዚህም እዚያም የሚታየዉን ችግር ለመፍታትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር ትብብሩ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት የህግ እና ፖሊሲ አማካሪ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ችግር ለመፍታት ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች በቸኛ መፍትሄ ሳይሆኑ አንዱ ተዋናይ ናቸዉ ያሉት አቶ ዘሪሁን ነገር ግን በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ችግሮች፣ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ፣ መቋጫ እንዲያገኙ ውትወታም ጥረትም እናደርጋለን ብለዋል።
በሀገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶችም ያለዉን የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች በቅረበት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታዉቀዋል።

በአቤል ደጀኔ

መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.